ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ብሄራዊ አባል የሆነ በህጻናት ደህንነት ጥበቃና ልማት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ከማናቸውም ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ እሳቤዎች ገለልተኛ የሆነ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተበት እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት ፣ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ አዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ የሚገኝ የልማት አጋር ድርጅት ነው፡፡ ኤስ.ኦ.ኤስ የህጻናት መንደር ባሕር ዳር ፕሮግራም ያገለገሉ ላፕቶፕ ፣ኮምፒውተር ፣ኮፒ ማሽን ፣ፍሪጅ ፣ቴሌቪዥን ፣ኦቭን ፣ካሜራ ፣ወንበር ፣ሸልፍ ወዘተ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳድር የሚፈልጉ ግለሰቦችንና ተቋማት ጨረታው ከወጣብት ቀን ጀምሮ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- ጨረታዉ ከግንቦት 25 ቀን 2017 ዓም እስከ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓም 8፡00 የሚቆይ ሲሆን የሚወዳደሩብትን የጨረታ ሰነድና የሞሉብትን ዋጋ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጅው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾችም ወይም ተወካዮቹ ባይኖርም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የመንግስት ታክሶች ፣ክፍያዎች እና የባለቤትነት ማስተላለፍ ክፍያዎች (ካለ) በገዥው ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች ሁሉንም ሎት ወይም የፈለጉትን ሎት ብቻ መርጠው ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ሎት ሁሉንም የእቃ ዝርዝሮች መሙላት የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚሞሉ ተወዳዳሪዎች ከተገኙ ከውድድሩ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ቢሮ ቁጥር 3 በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- አሽናፊ ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሸናፊዎች በተጠቀሰዉ ቀን ካልከፈሉ ድርጅቱ የራሱን አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ ባሉት ሁለት ቀናት ውስጥ የከፈሉበትን ዕቃ ማንሳት አለባችው፡፡
- ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ፡- ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደር ባሕር ዳር ፕሮግራም ሽምብጥ ቀበሌ /ቀበሌ 13/ ካቶሊክ ታክሲ መያዢያ መጫረሻ አካባቢ ነው፡፡ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 49 70/ 058 226 49 77 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች