በምዕራብ ጐጃም ዞን የቡሬ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ሎት 1 ቧንቧና መገጣጠሚያ እቃዎችን እና ሎት 2 የሙያ ግዥ የሂሳብ ባለሙያዎችን የ3 ዓመት የተቋሙ የፋይናንስ እንቅስቃሴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስመርመርና መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሞሉትን ጥቅል ዋጋ 5 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የሚገዙት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ሲሆን ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ቡሬ ግ/ፍ/ን/ የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት እና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ተኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ 3፡10 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠ ነው፡፡
የቡሬ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት