የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመቄት ወረዳ እንስሳት ሀብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ ፈንድ በጀት በሎት ድምር ለእንስሳት ህክምና አገልግሎት የሚውል መድሃኒት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር ለምትፈለጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡-
- ቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የሙያ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- ግዥው ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችሉ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ካላንደር ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ቀጣይ ባሉት የሥራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ በሰም የታሸገ ቢሆን ይመረጣል ባለመታሸጉ ግን ጨረታውን ውድቅ አያደርገውም፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ከ06/12/2016 ዓም ጀምሮ እስከ 20/12/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ21/12/2016 ዓም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ የማይመለስ 00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ለሁሉም ሰነዶች በመክፈል መግዛት የምትችሉ ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ የሚገባው ግ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 211 00 91 ወይም 033 211 00 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት