በአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የተሸከርካሪ ኢንሹራስ ዋስትና አገልግሎት ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎቶችን ዓይነትና የተሸከርካሪዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ግዥ ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 37 ዘወትር ከ02/10/2017 ዓ.ም እስከ 16/10/2017 ዓ.ም ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳሩበት ኢንሹራንስ ዋስትና ሽፋን አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሸገዉ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 37 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 37 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 08 58 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡ አድራሻ ባ/ዳር ቀበሌ 08 ባ/ዳር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 37
በአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ