ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል/ት/መምሪያ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በደባይ ጥላት ግን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የቁይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተቋርጦ የቆየውን G+2 ባለ 15 ክፍል የመማሪያ ህንፃ ግንባታ በአልማ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች፡-

  1. ከላይ በተጠቀሱት የሥራ ዘርፍ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የሚገነባውን ግንባታ የያዘ ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 11፡30 ድረስ መውሰድ ይኖርባቸውል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ 31ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ለግንባታው የሚያስፈልገው የሙያ ብቃት ደረጃ 6 Bc ወይም 7 Gc እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈው ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም /በሲፒኦ/ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡ ነገር ግን የሞላው ዋጋ ከመሀንዲስ ግምቱ 25 በመቶ ዝቅ ብሎ የሞላ ተጫራች የውል ማስከበሪያ 25 በመቶ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ የሰጠ መሆኑ ታውቆ ለሁሉም አይተሞች በዋጋ መሞላት ይኖርበታል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፖስታ በደ/ጥ/ግ/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፈል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወተር በሥራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
  12. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ጥ/ግ/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ31ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በአል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ጨረታው ውድቅ እንደሚደረግ አውቀው በጥንቃቄ እንዲሞሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here