የዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የ2015 እና የ2016 በጀት ዓመት ከሀምሌ 01-11-2014 እስከ 30-10-2016 ዓ.ም የ2ዓመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች በግልፅ ጨረታ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር ከፍለው የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ የሚሰጡ ከሆነ)፡፡
- የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ፣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ከፍለዉ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ ፣የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል::
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ስዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ3፡30 በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 4 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎ በስልክ ቁጥር 0918710156 ወይም 0918710153 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡
የዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት