ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
76

የግልጽ ጨረታ ቁጥር አብክመ /ውኢቢ/ ግጨ/ዕግ/ቁጥር-003/2017

በአብክመ የውኃና ኢነርጅ ቢሮ በመንግስት ኢመርጀንሲ የበጀት ድጋፍ ሎት 1. የሹምሻሃ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት መገጣጠሚያ የኤሌክትሮ መካኒካል መገጣጠሚያ ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ ፣ሎት2. የደጀን መጠጥ ውኃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የኤሌክትሮ  ቧንቧ፣ መገጣጠሚያና የኤሌክትሪክ ኬብል ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ፣ሎት3. የወይን እናት መጠጥ ውኃ ተቋማት ጥገና ፕሮጀክት የመገጣጠሚያ፣ ቫልቭና አክሰሰሪ ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ ፣ሎት4. የመሻህ የገጠር መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የኤሌክትሮ መካኒካል ቧንቧና የመገጣጠሚያ ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ እና ሎት5. ለደብረ ማርቆስ ከተማ  የኤሌክትሮ መካኒካል ጠላቂ ፓምፕ፣ የራይዘር ፓይፕና የመገጣጠሚያ ዕቃዎች የዕቃ አቅርቦት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ለማቅረብ በዘርፉ(የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎች አቅራቢነት) ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀና ኢነርጅ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000/አንድ ሽህ/ ብር ብቻ በመክፈል በአብክመ የውሃና ኢነርጅ፣  ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 27 ማግኘት ይቻላሉ፡፡
  6. ተጫራቶች ለሚያቀርቡት እቃ ለሎት1. 100,000 /አንድ መቶ ሺህ / ብር፣ ለሎት2. 150,000 /አንድ መቶ አምሳ ሺህ/ ብር፣ ለሎት 3. 50,000 /አምሳ  ሺህ/ ብር፣ ለሎት 4. 50,000 /አምሳ ሺህ /ብር እና ለሎት5. 50,000 /አምሳ ሺህ/ ብር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ  ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ /ሲፒኦ// ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ከሰኔ 16/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ ሀምሌ 1 /2017 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን በዚሁ ቀን 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ  መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ /ቅጽ/ መሰረት መሞላት ይኖርበታል፡፡
  9. ሌሎች ተጫራቶች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251582-26-24-60 / +251 582-20-08-55 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡

 

የአብክመ ውኃና ኢነርጅ  ቢሮ

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here