የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/06/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሲቪል ስርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን /ፑል/ ፣ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ጨምሮ ለ2 መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት አመታዊ የቢሮ ህንፃ እና ምድረ ግቢ የጽዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ በኮንትራት ግዥ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታዉ የሚሳተፉ በአነስተኛና ጥቃቅን ኢተርፕራይዝ ተደራጅተዉ ከትምህርትና ስልጠና ተቋም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጥቃቅን የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣት ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከአነስተኛና ጥቃቅን ኢተርፕራይዝ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን አስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
- ሁሉም ተወዳዳሪዎች በጥቃቅን የተደራጁ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አዲስ ከተቋቋሙት ኢንተርፕራይዞች ዉጭ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን/ፑል