ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

የአብክመ ሥራ አመሪር ኢንስቲትዬት ለ2018 በጀት ዓመት በግቢው ውስጥ ለሚሰጠው ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የምግብ ግብዓት ሎት 1 የከብትና የበግ ስጋ ፣ሎት 2 እንቁላል ሎት 3 አትክልትና ፍራፍሬ ፣ሎት 4 ጤፍ ፣ሎት 5 የታሸገ የማዕድን ውሃ ፣ሎት 6 ፊኖ ዱቄት ሎት 7 ኬክና ቆሎ ፣ሎት 8 የባልትና ውጤቶች ፣ሎት 9 ሸቀጣሸቀጥ ፣ሎት 10 በርበሬ ፣ሎት 11 የማገዶ እንጨት እና ሎት 12 ቅመማቅመም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር አመታዊ ውል ተይዞ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም አገልግሎቱን ለማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን / ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያ በጋዜጣ /ኦንላይን/ ከወጣበት ቀን ከሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዬቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዪቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኔ 16 ቀን 2017 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ታሽጎ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በስራ አመራር ኢንስቲቲዬት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  11. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. ኢንስቲትዬቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ዝቅተኛ ድምር ዋጋ ነው፡፡
  13. ኢንስቲትዬቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሥራ አመራር ኢንስቲትዬት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here