የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሰ/ምዕ/ሪጅን/ትራ/ሰብ/ኦፕ ጥገና ቢሮ ለሳብስቴሽን እና ለትራንስሚሽን ጥገና፣ ለቅድመ ጥገና እና ለአስቸኳይ ሥራ ሰርቪስ አገልግሎት የሚውል የሚኒባስ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ዋስትና 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ /ከ90 ቀን በታች የሆነ ባንክ ጋራንት ተቀባይነት የለውም/
- ተጫራቾች የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ዝርዝር ጉዳዩን የያዘ ሰነድ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰ/ምዕ/ሪጅን ትራ/ሰብ/ኦፕሬሽን ከፖሊ ወደ ጋንቢ በሚወስደው መንገድ ከፍትህ ቢሮ አለፍ ብሎ በሚገኘው ህንፃ 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልጽ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም የተወዳደሩበትን ከፖሰታው ላይ በትክክል በመግለፅ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 06/12/2016 ዓ.ም እስከ 24/12/2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ለማገልገል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ከቀኑ 8፡30 የኢትዬጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ይከፈታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 65 09/ 058 222 08 29 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ከመሥሪያቤቱ ጋር ማሸነፉ በተገለፀለት በ5 ቀን ውስጥ ውል መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሰ/ምዕ/ሪጅን