የምዕራብ በለሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓ.ም ለምዕራብ በለሣ ወረዳ ት/ጽ/ቤት በአልማ በጀት ለአርባያ ከተማ የአፀደ ህፃናት መማሪያ ብሎክ 1 /አንድ ብሎክ/ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች /ድርጅቶች/ እንድትወዳደሩ እየጋበዝን፡- ስለሆነም በዚህ መሠረት ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ፡-
- በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ደረጃ 8 የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን 23/10/2017 ዓ.ም እስከ 22/11/2017 ዓ.ም ለተከታታይ 30 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ሥርስ ድልዝ ሣይኖረው በመሙላት በሁለት ፖስታ ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጉልህ በፖስታው ላይ በመፃፍ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ክብ ማህተም ፣አድራሻ ፣ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ምዕ/በ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሣጥን በ23/11/2017 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ በ4፡30 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከፊት ለፊቱ ልዩ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርባቸል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋጋጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ ምዕ/በ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለእለት ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሠኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሠነድ ጋር አያይዞ ጨረታ ሣጥኑ ከኦርጅናል ሠነድ ጋር ማስገባትአለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጨረታ ውጤት ከታወቀ የመድን ድርጅት የሚቀርብ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ በባንክ ቸክና ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ ምዕ/በ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 09 18 71 19 47 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው በክልሉ ገ/ኢ/ል ቢሮ ባወጣው የግዥ መመሪያ የሚተዳዳር ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ምዕ/በ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ከረዳት ገንዘብ ያዥ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
የምዕራብ በለሣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት