በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት አመት በኮሌጃችን ዉስጥ ያሉ ተሸከርካሪዎችን ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸው እና ደረጃ ሁለት እና ደረጃ ሶስት የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- አጠቃላይ የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚጠገኑ የመኪና ፓርቶች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 04 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት የሚሞሉትን ማንኛውንም ግብር ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ዋናውን ወይም በኮሌጁ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ኮፒ ሆኖ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በአማርኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በኮሌጁ የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በአስራ ስድስተኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 04 በዚሁ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል /ዝግ / ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 07 71 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ ከፈለገ ሒወት ሪፈራል ሆስፒታል 100 ሜትር ገባ ብሎ ከኦክስጅን ማቀነባበሪያ ጎን ይገኛል፡፡
የባሕር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ