የምዕራብ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች ከመደበኛ በጀት ለምግብ አገልግሎት የሚውል እህል እና የባልትና ዉጤቶችን አጫርቶ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን በሎት አንድ የምግብ እህል 1.ቀይ ጤፍ ፣2. በቆሎ ፣3. ነጭ ሌሌ ማሽላ ፣4. ጅሁላ ማሽላ ፣5. ደበር ማሽላ እና በሎት ሁለት የባልትና ዉጤቶች ማለትም 1. የተዘጋጀ ሽሮ ፣2. የምግብ ዘይት ፣3. የምግብ ጨዉ ፣4. እርሾ ፣5. ጎመንዘር ፣6. ባቄላና አተር ክክ እና 7. በርበሬ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ የሆነዉን አቅራቢ ድርጅት ለ9 ወር ከነሃሴ 1 ቀን 2017 እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ዉል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ /የቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የሚገዙ የህል አይነትና የባልትና ዉጤቶች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የህል አይነትና የባልትና ዉጤት 1.5 በመቶ /በሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመሂ 1 ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ከ23/10/2017 ጀምሮ እስከ 07/11/2017 ቀን ድረስ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉኃ ማረምያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን በመቅረብ ከ1-3 ያሉ ሰነዶችን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መዉሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ከ1-3 ያለው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ15 ቀን በጋዜጣ ላይ ቆይቶ በ16 ኛው ቀን ማለትም 08/11//2017 ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ዉ/ኃ ማረምያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ስለሆነ ሁሉንም በሎት 1. የተቀመጠዉን የእህል ዋጋ እና በሎት 2. የተቀመጠዉ የባልትና ዋጋ ለየራሳቸዉ መሙላት አለበት ካልተሟላ ግን ከጨረታ ወጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ የምግብ እህሉን እና የባልትና ዉጤቶች ምዕ/ጎ/ዞን ገ/ዉኃ ማረምያ ቤት ንብረት ክፍል በዝርዝሩ መሰረት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ ዋጋ እንዲሁም የማይነበብ ሥርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ የምግብ እህል እና የባልትና ዉጤት አቅርቦት 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆና፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 327 03 39 በመደወል እንዲሁም አማራ ሚዲያ ኮረፖሬሽን በታተመዉ በኩር ጋዜጣ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ በምዕ/ጎ/ዞን ዐቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ እስከ 40 ቀን ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
ምራብ ጎደር ማረሚያ ቤት መምሪያ
ገ/ዉኃ