ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ሜዲካል ኦክስጅን እና የመድሀኒት የደረቅ ጭነት ማጓጓዣ መኪና ኪራይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም  ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁ /ቲን/ ሰርተፊኬት እና ለሜዲካል ኦክስጅን ሜዲካል ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን  የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ  ከጨረታ  ሰነዱ ጋር አያይዘው  ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር  መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/  እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር  ዘወትር በሥራ ሰዓት  ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን  ቢሮ ቁጥር 3  የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት  በልዩ ልዩ  ምክንያት  በሚመለከታቸው የመንግስት  ተቋማት  ያልታገዱ  መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማንኛውንም   የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ  የጨረታ ሰነዱ  በፖስታ ታሽጎ   የድርጅቱ ክብ  ማህተም ፤ፊርማ እና አድራሻ  በማስቀመጥ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ  ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ  የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ  ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ /  ለሜዲካል ኦክስጅን ለሚወዳደሩበት እቃ  የሚሞሉት ጠቅላላ  ድምር ማንኛዉንም ግብር ጨምሮ አንድ በመቶ እና  የመድሀኒት የደረቅ ጭነት ማጎጓዣ መኪና ኪራይ  ብር 10,000 /አሰር ሽህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ  የክፍያ ትዕዛዝ  /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ወይም በሆስፒታሉ ገቢ ደረሰኝ መሂ-1   ገቢ በማድረግ  ከፖስታው ውስጥ  አብሮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ የዉል ማስከበርያ  ዋስትና  ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ  ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት  በ8፡30  ተጫራቾች  ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት  ባይገኙ  ግን ፕሮግራሙ  የማይስተጓጎል  ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች እቃዉ እስከ እንጅባራ ጠቅላለ ሆስፒታል ድረስ በራሳቸዉ ወጪ  በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ  በሚቀጥለው  የመንግስት የሥራ ቀን  በተጠቀሰው  ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here