በአማራ ገጠር መንገዶች ኮን/ኤጀንሲ የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ አሮጌ ተመላሽ ጎማ ፣ባትሪ ፣በርሚል ፣ካለመዳሪ እንዲሁም ፍላፕ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡- ሎት 1 ያገለገሉ ጎማ ፣ሎት 2 ባትሪ ፣ሎት 3 በርሚል ፣ሎት 4 ካለመዳሪ /ውስጥ ላስቲክ/ እና ሎት 5 ፍላፕ ስለዚህ፡-
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም አካል በጨረታው መሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ቢሮ ቁጥር 19 በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ ጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ስም ደረሰኝ በማስቆረጥ ጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን /መጫረቻውን/ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር ከሰኞ እስክ አርብ በሥራ ሰዓት እንዱሁም ቅዳሜ እስከ 6፡30 ከ23/10/2017 ዓ/ም እስከ 08/11/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ08/11/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ቢሮ ቁጥር 19 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ሆኖ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሊሸጥ ከተዘጋጀው የንብረት ወይም የዕቃ ዓይነት ከተገለጸው መጠን ብዛት ቀንሰው መወዳደር አይችሉም ፣ሁሉንም ንብረቶች ማንሳት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ፖስታቸው ላይ ስም ፊርማ ስልክ ቁጥራቸውን መጻፍ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 891 18 99 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
ደ/ማርቆስ