የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት በአውትሶርስ የሚሰሩ የጽዳት አገልግሎት ፣የአትክልት ማስዋብና የጉልበት ሥራ ፣የተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት የግቢ ጥበቃና ሴኩሪቲ አገልግሎት እና የህመምተኞች የልብስ እጥበት አገልግሎት ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፡-
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
- ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉን በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበት የአገልግሎት ዋጋ ድምር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ 2 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በመመሪያው መሰረት ቫት ይሰበስባል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት አገልግሎቶች 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን አገልግሎት ዋጋ፣ 1 በመቶ በጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ በማሲያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 259 ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራችው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራሣቸውን ማግለል አይቻልም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ30/10/2017 ዓ.ም እስከ 20/11/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ20/11/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስራ ሂደቱ ስልክ 033 331 01 72 ደወሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ውድድሩ በሎት ድምር ነው፡፡
- በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ማህበራት ካሉ ነጥብ አሰጣጡ በመመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- የጨረታ ጊዜው ውሉ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ነው፡፡
የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል