በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የበላይ ዘለቀ ክ/ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ መስተንግዶ፣ ህትመት እና ኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ የጨረታ የግዥ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- በስማቸው የታተመ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰረተ /ሲፒኦ/ የሞሉትን ዋጋ አንድ በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የድርጅቱ ሕጋዊ ማህተምና የሞላው ሰው ስምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በአጠቃላይ በዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢነት መረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የእያንዳንዳቸው ሎቶች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያቀረቡትን /የሞሉትን/ ዋጋ በፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 06 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከ06/12/16 ዓ.ም እስከ 26/12/2016 ዓ/ም ድረስ በግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 06 ዘውትር በሥራ ሰዓት የሚቆይ ሆኖ በ27/12/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 እጩ ተወዳዳሪዎች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 226 58 52 ወይም በበላይ ዘለቀ ክ/ከተማ ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ማሳሰቢያ፡- የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል እና ተቋሙ ድረስ መጥቶ አገልግሎት መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡
የበላይ ዘለቀ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት