ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
65

የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት እስከ 30/10/2018 ዓ/ም አጠቃላይ የቢሮና የግቢ ፅዳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻያል በአንድ ፖስታ እና ቴክኒካሉን በሌላ ፖስታ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለቢሮ እና ግቢ ፅዳት ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 30,000 /ሰላሣ ሺህ / ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከ7/11/2017 እስከ 21/11/2017 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀናት ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን በ22/11/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይቻላሉ፡፡

የአብክመ ፍትህ ቢሮ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here