በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የመገናኛ ሁለ/የገበ/ኅ/ሥራ ማህበራት ዬኒየን ኃ.የተወሰነ የሰራተኛ ደንብ ልብስ 1ኛ. ሎት /ምድብ አንድ የተለያየ አይነት የተዘጋጀ ደንብ ልብስ ፣ሎት 2ኛ. /ምድብ ሁለት ብትን ጨርቅ እና 3ኛ. ሎት /ምድብ ሶስት/ ጫማ በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 2 በመቶ በባንክ /በሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋሰትና/ አስይዘው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡ ከዩኒየኑ በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ የሚያሲዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ /ቫትን/ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ /ቫት/ የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዬኒየኑ ፋይ/ግ/ንብ/አስ/ ክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይሰጣል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደንብ ልብስ አቅርቦት ግዥ የጨረታ ሰነድ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖራው የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋውን ሞልተው በፖስታ አሽገው ከዬኒየኑ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በወቅቱ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተወዳዳሪ የሚለየው በሎት /ምድብ/ ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሆኑ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም የደንብ ልብስ አይነቶች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ተጫራቹ መሙላት አለበት፡፡
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10 ኛው ቀን 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን በ10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ /በሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ አስይዞ በ5 ቀን ውስጥ ከዬኒየኑ ቀርቦ ውል መውስድ አለበት፡፡
- አሸናፊው ተወዳዳሪ ያሸነፈበትን የደንብ ልብስ ደብረታቦር ከተማ ከዩኒየኑ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ዪኒየኑ ያወጣውን ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ቅዳሜ ከሰዓት በፊት እስከ 6፡30 ድረስ የዩኒየኑ የሥራ ቀን ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 141 99 27 እና 058 441 13 36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- አድራሻ ፡-ደ/ታቦር ከተማ ጸደይ ባንክ ዋናው ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ነው፡፡
መገናኛ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተወሰነ