ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
62

በማዕላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሥር ባሉት የፑል ንብረት ክፍል ያሉ ቁርጥራጭ ብረቶችና የመኪና ቦዲ ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ከጽ/ቤቱ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ 14/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እና በ16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም ከ60 (ስልሳ) ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ የተቆረጠ በመምሪያው ሥም ማሥያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን /መጫረቻውን/ ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 05 በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሣሣይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ቦታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ንብረቶች በአሉበት ንብረት ክፍል በመሄድ በአካል ማየት ይቻላል፡፡
  9. ጨረታውን አሸናፊ የሚሆነው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ፖስታቸው ላይ ሥም ፊርማ ፣ሥልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 336 448 ወይም 09 09 36 76 39 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ገንዘብ ት/ቤት ይገኛል፡፡

የጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ገንዘብ ት/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here