ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
75

ድርጅታችን መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ ሎት 1. ጀንፈል ሩዝ (ቀይ እና ነጭ) 2470 ኩ/ል ፣ጓያና ሽምብራ 86 ኩ/ል ፣በድምሩ 2566 (ሁለት ሽህ አምስት መቶ ስልሳ ስድስት) ኩ/ል ሰብል እና ሎት 2. ያገለገለ ሱዚክ ሞተር ሳይክል በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፡-የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዚህ ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ሥም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን እና ተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳብር) መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል በመግዛት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን ሰነዱን በመግዛት ዋጋቸውን ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት  ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተሽጦ በ11ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ምርቱ በዩኒዬኑ መጋዘን ደ/ታቦር ኢንዱስትሪ መንደር ባለው መጋዘን ማየት ይችላሉ፡፡
  7. አሸናፊው ሰብሉን የሚረከበው በዩኒዬኑ መጋዘን ሲሆን የትራንስፖርትና የወዛደር በግዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ከፍተኛ የሞላው ሲሆን አሸናፊው በተለየ በ5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅበታል፡:
  9. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 28 64 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here