ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት ፣በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ስለሆነም የማህበሩን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል፡-

  1. የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ፣የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር ከፍለው የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱ፡፡
  3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋና ኦዲት መሥሪያ ቤት (ቢሮ) ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በአማራ ልማት ማህበር ባሕር ዳር ከተማ ዋናዉ መ/ቤት በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በአማራ ልማት ማህበር ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር 108 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ሥራ ቀናት ዉስጥ በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  8. ጨረታዉ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ ፣የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ ማስገባት አለባቸው ፤ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም አሸናፊ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  10. ማህበሩ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አማራ ልማት ማህበር (አልማ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here