የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ለራሱ ለፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን እና ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የተሽከርካሪ መለዋወጫና ጌጣጌጥ ዕቃዎች አቅርቦት ፣የተሽከርካሪ መድህን ዋስትና ፣የተሽከርካሪ ጥገና ፣የኤሌክትሮኒክስና የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች ጥገና እና አውት ሶርስ የቢሮ ጽዳት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሚገዙ ዕቃዎች /አገልግሎቶች/ ግዥ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ /አገልግሎት/ ግዥ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ /አገልግሎት/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ (ANRS Plan and Development Bureau) በሚል ስም በማሰራት ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠው ለተሽከርካሪ መለዋወጫና ጌጣጌጥ ዕቃዎች በነጠላ ዋጋ ሲሆን ለሌሎች አገልግሎት ግዥ በጠቅላላ ዋጋ ድምር ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ
ባሕር ዳር