የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ዉስጥ ባሉ ንብረት ክፍሎች ዉስጥ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛዉም ግለሰብ /ድርጅት/ በጨረታዉ የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ ከወረዳዉ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 02 በመክፈል ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት እና በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የእቃ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም ከ60 ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰተ የባንክ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ የተቆረጠ በወረዳዉ ስም ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን /መጫረቻዉን/ ዋናዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 03 በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በተዘጋጅዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለጸዉ ቦታ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ንብረቶች ባሉበት የንብረት ክፍል በመሄድ በአካል ማየት ይቻላል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነዉ በከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ፖስታቸዉ ላይ ስም ፣ፊርማ ፣ስልክ ቁጥር መጻፍ አለባቸዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ 058 270 01 95 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት