አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት ፣በጤና ፣በሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአደጋ ምላሽ ሥራዎች ዙሪያ ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ከዩኒሴፍ /ኤፍሲዲኦ ጋር በመተባበር ለሚተገብረው Ethiopian Crises to Resilience (EC2R) Program to Support Emergency Affected Pro-primary and Primary School Girls and Boys Including Children with Disabilities in Habiru, Gidan, Abergello and Telemet woredas in Amhara ፕሮጀክት የትምህርት ቤቶች ገቢ ማስገኛ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ገዝቶ በአራቱም ወረዳዎች ጠለምት ፣አበርገሌ ፣ሀብሩና ግዳን ወረዳዎች ሥር ፕሮጀክቱ ላተፋቸዉ ት/ቤቶች በአቅራቢዉ በኩል ማሰራጨት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከገንዘብ ያዥ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ ከሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/
ባሕር ዳር