በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለ4ቱም ፑል ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 የመኪና ጎማ ከነካለማደሪያ ፣ለግብርና ል/ጽ/ቤት አገለግሎት የሚወል ፣ሎት 2 የአቮካዶ ዘር ከነስጋው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለዉ መነበብ መቻል አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000 (ሶስት ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከ28/11/2017 ዓ.ም እስከ 13 /12/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ በ13/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት /ባይገኙም/ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜዉ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየዉ በሎት /በድምር ዋጋ ነዉ/፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠዉ ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀዉ ስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግደታ አለበት፡፡
- ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት በሎት 1 የተጠቀሰውን የመኪና ጎማ ከነከለማደሪያ ተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት እንዲሁም በሎት 2 የተጠቀሰውን የአቮካዶ ዘር ከነስጋው ከሐይቅ ከተማ 7 ኪ/ሜትር ከሚገኘው ጃሪ ችግኝ ጣቢያ ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍሉ አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታዉን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት