ቁጥር 1/2018
በአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት አመት ሎት 1 የመኪና አመታዊ ጥገና ፣ሎት 2 የመፅሄትና ጋዜጣ ግዥ እና ሎት 3 የአንሶላ ፣ብርድ ልብስ የመኪና ወንበር ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ እና ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከግዥ ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 33 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ (ቢድ ቦንድ) በጨረታ ሠነዱ የተገለፀውን የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይኖርባቸዋል። ጨረታዉም በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 10 68 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 20 30 /058 220 10 81 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
ባሕር ዳር