ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
92

የግዥ መለያ ቁጥር መ/ግ/01/2017

በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን MESOB አንድ ማዕከል አገልግሎት የሚከተሉትን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ግዥ  አወዳድሮ ለመግዛት  ይፈልጋል፡፡

  • Network Computing and storage
  • Modular data Center
  • Digital Signage and Screens
  • Counter Area Technologies
  • IP Surveillance System ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ  ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል በተለያየ ፓስታ በማሸግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከሐምሌ 24/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት እና በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44 /058 220 96 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here