በቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በወረዳው ለሚገኙ ሴ/መስሪያ ቤቶች ለ2018 የበጀ ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 መኪና መለዋወጫ እቃዎች ፣ ሎት 2 መኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዎችን ለይቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚፈለጉትን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊክሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና በመሂ 1 በጥሬ ገንዘብ የተቆረጠ ደረሰኝ ኮፒ አድርገው በፖስታ አሽገው ማስገባ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቋራ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ከ28/11/2017 እስከ 12/12/2017 ዓ.ም 12፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቋራ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥኑ በቀን 13/12/2017 ዓ/ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቋራ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በቀን 13/12/2017 ዓ/ም 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸው የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስ/ቡድን ወይም ቋራ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 058 271 00 31 /02 69 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ሎት 1 መኪና መለዋወጫ እቃዎችን በ13/12/2017 ዓ/ም 3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል ፤ሎት 2 የመኪና ጎማ በ13/12/2017 9:30 ታሽጎ 10:00 ይከፈታል አሸናፊው ድርጅት የመኪና ጎማውን የቋ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ድረስ ማምጣት አለበት፡፡
የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት