የምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት ለዞን መምሪያዎች በመደበኛ በጀት በሎት (ምድብ) የተለያዩ አቅርቦቶች ሁነው ተዛማጅ ወይም ተቀራራቢ ባህሪና ጠቀሜታ ያላቸውን አንድ አይነት የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ከተሰጣቸው አቅራቢዎች ሎት 1. የመኪና እቃ መለዋመጫ ፣ሎት 2. የመኪና ጎማዎች እና ሎት 3. የመኪና የሞተር ዘይትና የተለያዩ ቅባቶች ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የኩንትራት ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ሎት 1. የመኪና እቃ መለዋመጫ ፣ሎት 2. የመኪና ጎማዎች ፣ሎት 3. የመኪና የሞተር ዘይት የተለያዩ ቅባቶች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዞኑ አድራሻ ምዕ/ጎንደር ዞን ገንደ-ውሃ ከተማ ከአቢሲኒያ ባንክ 3ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ መሂ1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ኮፒ ሆኖ የጠቅላላ ግዥውን ዋጋ 2 በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ግዥን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ ማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስከበሪያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱን ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታውን ለመገምገም በርካታ ጊዜ ለማይወስዱና ውስብስብ ላልሆኑ ግዥዎች ከ40 ቀናት መብለጥ እንደሌለበት አውቀው የመጫረቻ ሰነድዎን መሙላት አለብዎት፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ ውል እስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ 20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕ/ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ከ28/11/17 ዓ/ም እስከ 12/12/17 ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው በ13/12/17 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በገንደ-ውሃ ከተማ በምዕ/ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል ድምር ስለሆነ የእያንዳንዱ ዝርዝር ዋጋ መሞላት አለበት ፤ካልተሟላ ግን ከጨረታ ውጭ የሚሆን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ከጨረታ ሰነድ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞላ ዋጋና ሥርዝ ድልዝ ያለበት እንዲሁም የማይነበብ ጽሑፍ ተሞልቶ ከቀረበ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚከፈትበት ስዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 331 08 80 /058 331 06 32 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ግዥ ፈፃሚ አካል የጨረታውን አሸናፊ በሚመርጥበት ጊዜ መለኪያዉ ተለይቶ የሚታወቅ እስከሆነ ድረስ በእያንዳንዱ የዕቃ መለኪያ የተሰጠውን የነጠላ ዋጋ ወይም ሌሎች የውል ቃሎች እና ሁኔታዎችን ሳይለወጡ የእቃውን ብዛት ወይም መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ መሂ1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ኮፒ በማስያዝ በምዕ/ጎንደር ዞን ዐቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም የምክንያቶቹን አግባብነት እንዲያስረዳ አይገደድም፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ