ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
36

የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የመኪኖች ኢንሹራንስ ዋስትና ፣የተሽከርካሪ ጥገና  እና የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው ፤ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ ፣በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ወይም ፍሉድ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የመኪኖች ኢንሹራንስ ዋስትና ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ፣ የተሽከርካሪ ጥገና ብር 3,000 /ሶስት  ሺህ ብር/ እንዲሁም የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ብር 28,000 /ሃያ ስምንት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሣ ብር) በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ገንዘብ ያዥ  ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማለትም ከነሐሴ 5/2017 ዓ.ም እስከ  ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍትህ ቢሮ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ተኛው ቀን በ20/12/2017 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡  ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ፍትህ ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here