ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

ቁጥር ውአገ/14699/5/35

የደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ድርጅት የ2017 በጀት አመት አቅርቦቶችን ሎት 1. የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች ፣ሎት 2. ከ2014 ዓ/ም እስከ 2017 ዓ/ም የሂሳብ ምርመራ አዲት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ  የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያቁጥር /ቲን /ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ  መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4  የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር  አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃወችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ  /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች  የጨረታ  ሰነዱን  የማይመለስ  ብር 100 /አንድ መቶ  ብር/ በመክፈል ከገ/ግ//ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር  8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር  ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/  ማስያዝ  አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም  ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጂዎች በጥንቃቄ  በታሸገ  ፖስታ ለመካነ ኢየሱስ ከተማ ውሃ አገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ለ15 ተከታታይ  ቀናት  ማስገባት ይችላሉ ፤በዚው ቀን 11፡00  ጨረታው  ይታሸጋል፡፡
  10.  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው  በተገኙበት በቢሮ ቁጥር  8 በ16ኛው ቀን  4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ  አማራጭ  ካገኘ ጨረታውን  በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ  መብቱ  የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለጨረታው  ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 03 02  በመደወል መረጃ ማግኘት  ይችላሉ፡፡

የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here