በአብክመ ማረ/ቤቶች ኮሚሽን ሥር የሰቆጣ ማረ/ቤት መምሪያ ለህግ ታራሚዎች ምግብ ዝግጅት አገልግሎት የሚውሉ 1. እህልና ጥራጥሬ ፣2. ሽሮ ፣በርበሬና ጨው ፣3. የማገዶ እንጨት እና 4. የዳቦ ዱቄት ፣ዘይትና የተለያዩ ለወጥ ማጣፈጫ የሚሆኑ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጥራጥሬ ጅምላ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በግልጽ በሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለምግቡ የሚያስፈልጉ የጥራጥሬ አይነቶችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሣ ብር) በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ5/12/2017 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ5/12/2017 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በ19/12/2017 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3:30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 01 14 ወይም 09 14 60 31 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ማረሚያ ቤት ቀበሌ 01 ነው፡፡
የሰቆጣ ማረ/ቤት መምሪያ