ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
39

የጨረታ ቁጥር 01/2017

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዓመታዊ የጽዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የሚወዳደርበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መመሪያውንና የጨረታዉን ዝርዝር ሁኔታ አጠቃላይ የእቃዎችን ዝርዝር የሚገልጽ  ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 009 ባ/ዳር መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፤የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከሠነድ ጋር አብሮ አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን በማስፈርና በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቬሎፕ ዋና እና ቅጅ ሰነዶችን ለየብቻ በማሸግ ለአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 013 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ3፡30 የሚዘጋ ሲሆን በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 226 89 65 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብከመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here