የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ ለምግብነት የሚውሉ ንፁህ በቆሎ ብዛቱ 17160.80 የሆነ ፣ያልተበጠረ ጤፍ ፣የተለያዩ ብጣሪዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ፣ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ የኢንተርኘራይዙ መሥሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላለ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስረከቢያ (ቢድ ቦንድ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተኘራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ሥምና አድራሻ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል ፤በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፤ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
- ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
- የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸው፡፡
- ያገለገሉ ጆንያዎችና ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርቡ አይገደዱም፡፡
- ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀው ውስጥ እንደ አስፈላጊነቱ መጠን እስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርኘራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 /09 18 01 69 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ