ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
121

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የማክሰኝት ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ከሎት 1. እስከ ሎት 6. ያሉትን ዝርዝር እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ሒሳብ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የውሃ የመገጣጠሚያ እቃዎች፣ ሎት 2. የጽሕፈት መሳሪያ፣ ሎት 3. የደንብ ልብስ፣ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ እቃ ገዥ፣ ሎት 5. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 6. ኦዲት ማስደረግ/ አጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሤ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  3. የጨረታ ዋጋ ከ50,000.00 /ከሃምሳ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የሚወዳደሩት ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ ለኤሌክትሮኒክስ እቃ አቅራቢዎች ግን ሁሉም የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1 እስከ 6 የተጠቀሱት የሚያስፈልጋቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሎት 1 እስከ 6 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ ብር/ ከ7/12/17 ዓ/ም እስከ 21/01/2017 ዓ/ም እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ለኦዲት ምርመራዉ የጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት ጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ውል ይፈርማል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከኦርጅናሉ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን በ22/12/2017 ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ ማስገባት የኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ እለት የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 3፡46 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ ታጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ከፈታል፡፡  ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፋ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የጽ/ቤቱ ሂሳብ የሚመረመረው የአምስት በጀት ዓመት ሲሆን አጠቃላይ ፕሮፋይሉን በተመለከተ ከጨረታ ሰነዱ መመልከት ይቻላል፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 332 01 50 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  14. የኦዲት ምርመራ አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በአቀረበው ጠቅላላ ዋጋ መሰረት አንደኛ የወጣው አሸናፊ ድርጅት ይሆናል፡፡
  15. ማሳሰቢያ፡- ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ድረስ በጽ/ቤቱ በሚያቀርበው ሳምፕል፣ ስፔስፍኬሽንና ናሙና መሰረት በማየት ዋጋቸውን መሙላትና ከአሸነፉም በኋላ ሳምፕሉ፣ በስፔስፍኬሽኑእና ናሙና መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከእያንዳንዱ ሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ ከፊል መሙላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡

የማክሰኝት ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here