በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በUNDP በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ለወላድ እናቶች አገልግሎት የሚውል የወላድ እናቶች አልጋ ፣ሎት 2. ሶላር መብራት ሎት 3. ለወላድ እናቶች ለመኝታ አገልግሎት የሚውል ፍራሽ አስከ ራበር ሽት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡፡፡
- የቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት የዕቃዎቹን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1.5 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማለትም በአማርኛ የተተረጎመ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከ05/12/2017 ዓ/ም እስከ 19/12/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ቀናት ከ05/12/2017 እስከ 19/12/2017 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 20/12/2017 ዓ/ም 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል ፤ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም ጨረታ የመከፈት ሰርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር (በሎት)ይሆናል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ማድረግ አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎቹን ርክክብ ጃናሞራ ወረዳ መካነ-ብርሃን ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ አምጥተው የሚያስረክቡ ሲሆን ትራስፖርትን እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት