ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
53

የጨረታ ቁጥር 1/001/05/17

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ከ30/12/2017 እስከ ሰኔ/30/2018 ድረስ የሚቆይ ለሆስፒታሉ ሰራተኞች ሰርቪሰ አገልግሎት የሚውል  ታታ ደረጃ አንድ 60 ወንበር  እና ከዚያ በላይ የሚይዝ መኪና በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ በዓቃቢ ህግ ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. መኪናው የሚፈልጋቸውን ወጭዎች ከናፍጣ ጀምሮ ሙሉ በሙ ባለንብረቱ (ባለሃብቱ) የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  5. ከነሐሴ 30/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ/ም ድረስ ውል ሊወስድ የሚችሉ፡፡
  6. የመኪና ሊብሬ ያላቸው ሆኖ ሆስፒታሉ ዝቅተኛ ዋጋ በሞላ ተወዳዳሪ  አሸናፊዉን  የሚለይ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ ፤ጨረታው ከወጣበት ከ05/12/2017 ዓ/ም እስከ  20/12/2017 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
  9. የጨረታው ሳጥኑ የሚታሸገው 20/12/2017 ከቀኑ 11፡30 ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሳንጃ የመ/ደ/ሆስፒታል አዳራሽ በ21/12/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር አንድ በመቶ ጠቅላላ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጀናልና ኮፒውን ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሳዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  13. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና ሌሎች አላስፈላጊ መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  14. አሸናፊ ድርጀት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  15. ሆስፒታሉ የሚገኛዉ ሰርቪስ ከሚጀምርበት ቦታ ጀምሮ 3 ኪ/ሜ ርቀት አለዉ ፤በመሆኑም ጠዋት 1፡50 ወደ ሥራ ፣ለምሳ  6፡30 ከምሳ መልስ 8፡20  እንዲሁም ማታ ወደ ቤት 11፡30 በድምሩ 4 (አራት) ዙር እና እሁድና ቅዳሜ 2፡30 ወደ ቢሮ 11፡30 ወደ ቤት በድምሩ (ሁለት) ዙር  ማመላለስ አለበት፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ለዋስትና የሚያዘው (ሲፒኦ) በቁጥርና በፊደል የተጻፈው የተለያየ ከሆነ ተቀባይነት የለውም ፡፡ለበለጠ መረጃ 09 18 19 85 88 /09 34 62 3 267 ደዉለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here