በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 ያገለገሉ አሮጌ ተመላሽ ጎማ እና ሎት 2 ያገለገሉ አሮጌ ተመላሽ የመኪና ባትሪ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ማናኛውም ተጫራች መሣተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 19 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ሥም ደረሰኝ በማስቆረጥ ጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች በጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን (መጫረቻውን) ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡30 ከነሐሴ 12/2017 ዓ/ም እስከ መስከረም 2/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን መስከረም 2/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 19 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በየሎቱ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሊሸጥ ከተዘጋጀው የንብረት ወይም የዕቃ ዓይነት ከተገለጸው መጠን (ብዛት) ቀንሰው መወዳደር አይችሉም ፤ሁሉንም ንብረቶች ማንሳት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በመወዳደሪያ ፖስታቸው ላይ ሥም፣ ፊርማ ሥልክ ቁጥራቸውን መጻፍ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 771 18 18 በመደወል እና መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጐጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት