ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
32

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ  ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በመደበኛ በጀት ማስፈፀሚያ ሎት 1 የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እንዲሁም ሎት 2 የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ የግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ዉል በመያዝ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ለሎት 1 በበጀት አመቱ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ/ም ዉል በመያዝ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመሥሪያ ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  6. ከዚህ በላይ የተቀመጡትን የመወዳድሪያ መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ክፍት ሲሆን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ላይ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መዉሰድ ትችላላችሁ፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን መ/ቤቱ ባዘጋጀዉ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዉስጥ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ብሎ በመለየት በአንድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ ዘወትር በሥራ ስዓት ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዱን ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
  8. አሸናፊ የሚለየዉ በእያንዳንዱ በወጣዉ ሎት በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት የዉል ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ የሚችል፡፡
  10. አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት ዉል የሚወስደዉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ይሆናል፡፡
  11. የእቃ እርክክብ ቦታ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ይሆናል፡፡
  12. ጨረታዉ በአስራ ስድስተኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  13. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. የጨረታ ሰነዱ በተዘጋጀዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሞላት አለበት፡፡ከነጠላ ዋጋዉም ሆነ ከጠቅላላ ዋጋዉ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታዉ ማህተም ከንግድ ሥራ ፈቃዱ ጋር በቀጥታ ተዛማጅ መሆን ይኖርበታል፡፡
  17. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቀጥር 04 በመምጣት መጠየቅ የሚቻል ሲሆን ወይም በስልክ ቁጥር 0900 41 59 24 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here