ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

በወልዲያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሎት 1  አቀስታ ፣መካነሰላም ፣ላሊበላ ከተማና ፍኖተ ሰላም ለሚሰራቸው የሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ የሚውል የአልሙኒየም በርና መስኮት ፣ታምቡራታ በር ፣ቲቪሲ በርና መስታወት አቅርቦትና ገጠማ  ፣ሎት 2 ለከሚሴ ሆስፒታል ግንባታ የሚውል የኤሌክትሪክ ማቴሪያል አቅርቦት ግዥ እንዲሁም ሎት 3 ለከሚሴ ሆስፒታል ግንባታ የሚውል የሳኒተሪ ማቴሪያል አቅርቦት ግዥ በዘርፉ በተሰማሩ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ ፣በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤የግር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ ፤ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) የባንክ ጋራንቲ ዋና (ኦርጅናል) ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም ፤ ቢቀርብም ተቀባይነትም የለውም፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ወልድያ ከተማ በሚገኘው ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ ፤የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን 11:00 ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፤ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
  4. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል ፤አሸናፊው በእያንዳንዱ ሎት ሳምፕል በማቅረብ የቀረበውም ሳምፕል በአማካሪ መጽደቁ ተረጋግጦ የአቅርቦትና የገጠማ  ሥራው በራሱ ወጭ ሳይት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ክፍያን በተመለከተ በሁሉም ሎቶች በአማካሪዎች በፀደቀው ሳምፕል መሰረት ቦታው ድረስ ማቅረብና መግጠም ሲችሉ ነው፡፡
  6. በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
  7. ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ በተዘጋጀው ሰነድ ብቻ መሙላት አለበት፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
  9. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here