የፍኖተ ሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ዕቃዎች ማለትም ሎት 1 -75 ኪሎ ዋት ሠርፈስ የዉሃ ፓምፖች እና ሎት 2 ኤክስትራክተር በግልጽ ጨረታ የግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በዉሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከ1-6 የተዘረዘሩትን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፤ በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል ፤በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር አራት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማስገባት አይቻልም፡፡
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊዉ ጋር ዉል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያዉ ይመለሳል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ለእያንዳንዳቸው ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በሥራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን የሎት ዕቃዎች ጠ/ዋጋ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) /በጥሬ ገንዘብ ለፍኖተ ሰላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት አስይዘዉ ዉል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ፍኖተ ሠላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸዉ፡፡
- ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ (ሎት) በማድረግ ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በጨረታዉ መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነትን አይወስድም፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 13 87 /00 75/ 09 23 4 26 123 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት