ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

በአብክመ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኜው መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒየን ኃ.የተ.ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሎት 1 የምግብ ጤፍ ሽያጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአሽናፊው መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ግልጽ ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው ፤እንዲሁም ዋጋ ሲሞሉ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት ፤ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታ ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሦሥት መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10 ተከታታይ ቀናት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ቅዳሜ የዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. ከአንድ ሎት ውስጥ ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም ፤አሽናፊ የሚለየው በተናጠል ይሆናል ፤አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል (ይሸፍናል)፡፡
  12. የምግብ ጤፍ ምርት (ሰብል) ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የወዛደር ማሳጫኛ እና የትራንስፖርት ውጪ በአሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል ፤የሰብሉ ብዛት እና የጥራት መጠን (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  13. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  14. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኜ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 10 63 46 46 / ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር ዩኒየን ኃ.የተ.

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here