ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
139

የአብክመ ሥራ አመሪር ኢንስቲትዬት ለ2017 በጀት ዓመት በግቢው ውስጥ ለሚሰጠው ስልጠና ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. ስቴሽነሪ፣ ሎት2. የጽዳት እቃዎች እና ሎት3. ግቢውን ለማፀዳት የአውትሶርስ ጽዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ሎት1. እና ሎት 2.በአንድ ጊዜ የሚቀርብ ሲሆን ሎት3. ከመስከረም 1/2017 እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ውል ተይዞ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን/አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያው በጋዜጣ /በኦንላይን/ ከወጣበት ከነሐሴ 13/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከነሐሴ 13/2016 እስከ ነሀሴ 28/2016 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ ነሐሴ 28/2016 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ ነሐሴ 28/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  11. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በድምር/በጠቅላላ ዋጋ/ ነው፡፡
  13. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ዐ58 226 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሥራ አመራር ኢንስቲትዬት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here