ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
106

የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ግዥዎች ማለትም ሎት 1 የተኝቶ ህክምና የበሰሉ ምግቦች ሎት ፣ ሎት 2 የጥበቃ ሥራ አገልግሎት ሎት 3. የጽዳት ሥራ  ፣ሎት 4 የነዳጅና ሌሎች ዘይት እና ቅባቶች እንዲሁም ሎት 5 የጭነት አገልግሎት ግዥ ህጋዊ አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ከሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት ሎቶችን በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ግዥዎች ለአንድም ዕቃ ዋጋ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመሄድ ለሁሉም ሎቶች የመጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በብር 50 (ሀምሣ ብር) ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለጥበቃ እና ለጽዳት ግዥዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አመታዊ ግዥዎች ጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ የምግብ እና የነዳጅ የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ሥም ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. የበሰለ ምግብ አቅርቦት አሸናፊዉ ሥራ የሚጀምረዉ ህዳር 10/2018 ዓ/ም  ይሆናል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል ፤እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  11. በጨረታው የጥበቃ እና የጽዳት አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የአመቱን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የነዳጅ እና የምግብ የዉል ማስከበሪያ ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና አገልግሎት እና እቃዎችን ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 058 775 00 16 /00 63 /10 16 እና ፋክስ ቁጥር 058 775 13 32 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here