ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
111

ቁጥር 04/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሎት 1. ለገንድ ዉሃ የኤፍ. ኤም ማሰራጫ ጣቢያ ግንባታ ከደረጃ 4 እና በላይ የሆኑ የህንጻና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ብቻ የሚሳተፉበት ፣ ሎት 2. ለአሚኮ ዋናዉ ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽና የቴሌቪዥን ህንጻ ኮርኒስ ሥራ ከደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ የህንጻና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሚሳተፉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት ይፈለጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት እና የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋናው ቢሮ ቁጥር 106  ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ለሎት 1. የቴክኒክ ምዘና ያለፉ ድርጅቶች ብቻ ወደ ፋይናንስ ዉድድር የሚገቡ ይሆናል ፤ሰነዱን በጥንቃቄ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በመሙላት የፋይናስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ ፤በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸዉ መ/ቤት የቅርብ ጊዜ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ም/ዳይሬክተር 1ኛ. ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል ፤ ሆኖም ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፤ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው በ22ኛው ቀን ሲሆን ዕለቱ ፤በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30  ይከፈታል፡፡
  7. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የግንባታ ሥራዎች ዓይነት ፣ቢል ኦፍ ኳንቲቲይ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው ቀርበዋል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ)

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here