ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የማዕከላዊ ጎንንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የእህል አቅርቦት እና የመኪና ጎማ፣ ሰርገኛ ጤፍ፣ ያልተከካ ነጭ በቆሎ፣ ባቄላ ክክ፣ ፊኖ ዱቄት፣ የተቀመመ በርበሬ፣ ጥሬ ጎመን ዘር እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. የሚቀርቡ የእህል አቅርቦት፣ የማገዶ እንጨት፣ የባልትና ውጤቶች እንዲሁም የጎማ አቅርቦት የማቅረቢያ ቦታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. አሸናፊው በየወሩ እንደ ህግ ታራሚው ብዛት አቅርቦቱ ሊጨምርም ሊቀንስም የሚችል ሲሆን እንዲያቀርብ መምሪያው በሚገልፀው በየወሩ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ከጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ማስታወቂያው በቀን ነሀሴ 26/2017 ዓ/ም በወጣው ጋዜጣ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከላዊ ጎንንደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከነሃሴ 26/2017 እስከ መስከረም 06/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሆነ ባይገኙም በስዓቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ መስከረም 06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 44 61 ወይም 09 64 79 28 60 በመደወል መረጃመ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here