የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር መኪና ላላቸው ተቋማት የተለያዩ የሞተር ዘይቶች እና ቅባቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ በተጠቀሰው የጨረታ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ያቀረቡት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውንን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሚወዳደረበት የዕቃዎችን ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ደብር ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ሥም ፊርማ፣ ማህተም ጨረታው ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለፅ በደ/ታ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ግዥ ንብ/ድን በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትብት እለት በዓል ቀን ከሆነ የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ሰዓቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመሰስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለፅ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከነጠላ ዋጋ ሆነ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች የሚሞላ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይችሉም፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንድም እቃ ሳይሟላ መቅረብ የለበትም ሳይሞላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- የእቃው መጠን አስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- መምሪያው በጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን ዓይነት የመግዛት መብት አለው፡፡
- እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሣሠቢያ፡- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በሥልክ ቁጥር 058 441 02 09 /058 141 93 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ