የቻግኒ ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፡፡ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ሰነዶችን ኮፒ ተደርገው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማያያዝ የሚችሉ፡፡
- የሚገዙ መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቦታ ቻ/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጤ/ጣቢያ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በ16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ጨርሰው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውን ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት እቃዎችን ጤና ጣቢያ የንብረት መጋዝን ድረስ በማቅረብ ጥራታቸውን ታይቶ በዝርዝር ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን 200.00 /ሁት መቶ ብር/ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የቻግኒ ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ