የኢትዮዽያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክምችት የሚገኘውን የምግብ እና የእህል ብጣሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈጋል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰአት በኋላ ከ7፡00 እስከ 10፡00 ባ/ዳር ቅ/ጽ/ ቤት በሚገኘው ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 / ሁለት መቶ /ብር መግዛት ይቻላል፡፡
- ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከ2በመቶ የማያንስ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው የስራ ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባ/ዳር ቅ/ጽ/ ቤት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- አድራሻ፡- ቀበሌ 16 ከጉደር አግሮ ኢንዱስትሪ ጀርባ ይገኛል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 66 09 /058 226 66 10 መደወል ይቻላል፡፡
የኢትዮዽያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት